Fana: At a Speed of Life!

ኮምቦልቻ፣ መካነ ሰላምና ባቲን ጨምሮ የባንኩ ቅርንጫፎች ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ሥር የሚገኙ አብዛኞቹ ቅርንጫፎች በአሸባሪው የህወኃት የሽብር ቡድን ዝርፊያና ውድመት የተፈጸመባቸው የባንኩ ቅርንጫፎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደረገ፡፡
በዚህም ኮምቦልቻ፣ ባቲ፣ መቅደላ፣ መካነ ሰላም ቅርንጫፎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 34 የደሴ ዲስትሪክት ቅርንጫፎች አስፈላጊው እድሳትና ቁሳቁስ ተሟልቶላቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ዘሩ ተኮላ አስታውቀዋል፡፡
የተዘረፉትን እና የወደሙትን ቅርንጫፎች በአፋጣኝ ወደ ሥራ ለማስገባት ባንኩ እያሳየ ባለው ቁርጠኝነት የአካባቢው ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ መሆኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዲስትሪክቱ በችግር ውስጥ የቆዩና እስካሁን ወደ ሥራ ገበታቸው ላልተመለሱ የዲስትሪክቱ የቅርንጫፍ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታችሁ እንድትመለሱም ጥሪ አቅርቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.