በደቡብ ሱዳን የተሰማራው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ጦር ግዳጁን በብቃት በመወጣቱ እውቅና ተሰጠው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ስር በደቡብ ሱዳን ታምቡራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ጦር የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት በመወጣቱ እውቅና ተሰጠው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ልዩ ተወካይ ኒኮላስ ሃይሶም ለሰላም አስከባሪ ጦሩ እውቅናውን ሰጥተዋል።
በተመድ የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ በሀገሪቷ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ከፍያለው ረጋሳ በላኩት ደብዳቤ፥ መቀመጫውን በያምቢዮ ደቡብ ሱዳን ያደረገው ጦሩ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር የሠላም ውይይቶችን በማካሄድ እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለተፈናቃዮች ጥበቃ በማድረግ ላሳየው የአርዓያነት ተግባር ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!