Fana: At a Speed of Life!

በጉራጌ ዞን በተፈጠረ ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖችን ወደ መኖሪያ ቀያቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ የሁለቱም ወገን ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያ ቀያቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
 
በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች ተፈናቅለው የቆዩ ነዎሪዎች ወደ ቀያቸው ሲገቡ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተገልጿል፡፡
 
በቀጣይም የአካባቢውን ሰላም የማረጋገጥና ቀሪ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ወደ ልማት የማስገባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው የተባለው፡፡
 
የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የፀጥታ አካላትና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
 
በሁለቱ ማህበረሰቦች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመቅረፍ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችንም የሚመለከታቸውን አካላት በማወያየት የእርቅ ስነስርዓት ለማከናወን ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸው ተጠቅሷል፡፡
 
ለተፈናቃዮች አቀባበል ሲደረግ የደቡብ ክልል አመራሮች፣ የዞን የስራ ሀላፊዎች፣ የወረዳና የከተማ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች መገኘታቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.