Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ጀምረዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት የሚቆየው ውይይት ፥ የተገኙትን ሁለንተናዊ ድሎች ጠብቆ የማስፋትና ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማሸጋገር ላይ ያተኮረ ይሆናል ተብሏል፡፡

“በዘላቂ ድል ወደ ብልጽግና የድህረ ጦርነት መዛነፎችና እርምጃዎች” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የተገኘውን ድል ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሰብአዊና የፀጥታ ፈተናዎችን በብቃት መፍታትና በአግባቡ መምራትም የውይይቱ አጀንዳዎች ይሆናሉ ነው የተባለውው።

በህልውና ጦርነት ሂደት ውስጥ ያገኘናቸው አገራዊ አንድነት ተናቦና ተቀናጅቶ የመስራት ልምድ በጋራ ዓላማ ለጋራ የመስራት ልምድ የአመራር ሁለንተናዊ ተሳትፎና ቁርጠኝነት ለአገራችን ዘላቂ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ የመምራት አስፈላጊነት ላይ ከፍተኛ አመራሩ በጥልቀት ይወያያል፡፡

በውይይቱ የድህረ ጦርነት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ የፀጥታና ሰብአዊ ሁኔታዎች በብቃት በመምራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.