በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 4 ሺህ 998 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ14 ሺህ 35 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሺህ 998 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት 10 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።
እንዲሁም 321 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ነው ያሉት።
260 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና ክፍል እንደሚገኙም ገልጸዋል።
በአጠቃላይ እስካሁን በኢትዮጵያ 415 ሺህ 443 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ 6 ሺህ 926 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!