Fana: At a Speed of Life!

ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በንጹሃን ላይ ጥቃት አደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አሸባሪው ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ጉንዶ መስቀል ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የዞኑ አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
 
የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ አብርሃም ብርሀኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት በሽብር ቡድኑ ላይ በመንግስት የተቀናጀ ማጥቃት እየተካሄደ መሆኑንና ቡድኑም ተስፋ በመቁረጥ ከመሸገበት ጫካ በመፈርጠጥ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ሸኔ ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ ቢልም ኦሮሞን እየገደለና ሀብቱን እያወደመ ይገኛል ያሉት ሀላፊው፥ በመንግስት በሚወሰድበት እርምጃ በመበታተን ላይ ይገኛል ብለዋል።
 
ትናንት ምሽት በዞኑ ኢዳቡ አቦቴ ወረዳ ባለበት ቦታ እርምጃ የተወሰደበት የሽብር ቡድኑ ወደ ደራ ጉንዶ መስቀል ወረዳ በመፈርጠጥ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንጹሀንን በየቤታቸው በመግባት ገድሏል ነው ያሉት።
 
በአሸባሪ ቡድኑ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ይቀጥላል ያሉት የአስተዳደርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሀላፊው፥ በአካባቢው ተጨማሪ ሀይል የተሰማራ በመሆኑ በአጭር ግዜ ውስጥ ይደመሰሳል ብለዋል።
 
አሸባሪው ሸኔ የኦሮሞን ህዝብ አንገት ለማስደፋት የሚሰራ ነው ያሉት አቶ አብርሃም፥ የአካባቢው ህብረተሰብና ሚሊሻው መግቢያ መውጫ እንዲያሳጣው ጠይቀዋል።
 
በአላዩ ገረመው
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.