በመዲናዋ ከ109 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከተማ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ሊጀመር ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ109 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከተማ ሴፍቲኔት እና የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ሁለተኛው ምእራፍ የፊታችን ሰኞ በይፋ እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ በከተማዋ 766 ሺህ ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ዜጎች እንዳሉ ተናግረዋል።
ከዚህ ውስጥ በመጀመሪያው ዙር 415 ሺህ ዜጎች የመርሀ ግብሩ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመጀመሪያው መርሀ ግብር ተጠቃሚ የነበሩ ከ49 ሺህ በላይ ዜጎችሠ እንደሚመረቁ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!