የገና በዓል በብሔራዊ ደረጃ በላልይበላ ይከበራል -የቱሪዝም ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የዘንድሮዉ የገና በዓል በልዩ ድምቀት በብሄራዊ ደረጃ በላልይበላ ከተማ እንደሚከበር የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ከአማራ ክልል መንግስት፣ ከአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ እና ከደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል ፡፡
በላልይበላ ከተማ የሚከበረው የገና በዓል እንደሀገር በኮረና ወረርሽንና በፀጥታ ችግር ተቀዛቅዞ የነበረዉን የቱሪዝም ዘርፍ ልማት እንቅስቃሴ እንደሚያነቃቃው ገልጸዋል፡፡
በክብረበዓሉ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገሪቱን ጥሪ ተቀብለው የመጡ የዳያስፖራ አባላት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የመገናኛ ብዙሃን ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!