ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 3 ሺህ 998 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 3 ሺህ 998 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት÷ለ11ሺህ 93 ዜጎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ነው 3 ሺህ 998 ዜጎች ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት 10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸውንም ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
በሌላ በኩል 410 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን÷337 ዜጎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ነው የገለጹት፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!