Fana: At a Speed of Life!

በተካሄደው ጦርነት መላው ኢትዮጵያዊያን መስዋዕትነት የከፈሉበትና ያሸነፉበት ነው – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን በሀገር ህልውና ላይ የደቀነውን አደጋ ለመመከት በተካሄደው ጦርነት መላው ኢትዮጵያዊያን መስዋዕትነት የከፈሉበት እና ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊውያን ያሸነፉበት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የሴቶች ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዘመቻ ህብረ ብሔራዊ አንድነት እና የተገኘው ድል፣ ከድል በኋላ የሚጋጥሙ ፈተናዎች እና የመፍትሄ መንገዶች እንዲሁም የተገኘውን ድል በሁለንተናዊ መስኩ ማስቀጠል ስለ ሚቻልበት ሁኔታ ከአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የሴቶች ተወካዮች ከአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት፥ በጦርነቱ መላ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈው መስዋዕትነትን ከፍለዋል፤ በውጤቱም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን አሸንፈዋል ነው ያሉት፡፡

በጦርነቱ በተገኘው ድል መዘናጋት አይገባም ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ በቀጣይ የተጀመረውን አንድነት አጠናክሮ ለቀጣይ ሁለንተናዊ ድል መነሳት እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡

በጦርነቱ የተገኘው ድል በህብረት በአንድነት ከተቆመ የማናሸንፈው ሀይል እንደሌለ ማሳያ ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡ ኢትዮጵያውያን በአንድነት በትውልድ ውስጥ አይበገሬነታቸው መቀጠሉን ያሳዩበት መሆኑን በመጠቆም፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የከተማዋ ሴቶች በተገኘው ድል ሳይዘናጉ መንግስት የሀገርን ህልውና ለማስከበር እና ሀገርንም ወደ ፊት ለማሻገር የሚያደርገውን ጥረት መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግንባር ተገኝተው ጦርነቱን መምራታቸው እና ድል ማስመዝገባቸው ኢትዮጵያውያንን ያኮራ ነው ብለዋል፡፡

የከተማዋ ሴቶች የአካባቢያቸውን ሰላም እና ጸጥታ በማስከበር እና በሌሎችም መስኮች የጀመሯቸውን እንቅስቃሴዎች ያለ መዘናጋት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ መቅረቡን ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.