Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ አካላት ለመከላከያ ሠራዊት ከ14 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ አካላት ለመከላከያ ሠራዊት ከ14 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ለአገር መከላከያ ሰራዊት የ10 ሚሊየን ብር የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ያስረከበ ሲሆን ÷ ከድጋፍ ውስጥ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሆነው ቀድሞ ግንባር ድረስ በመገኘት በዓይነት አድርጓል፡፡

ዛሬም ድርጅቱ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሚኒስቴር ርክክብ መፈጸሙን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በተመሣሣይም በምዕራብ ኦሞ ዞን የመኤኒ ጎልድያ ወረዳ አስተዳደርና የባቹማ ከተማ አስተዳደር ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አበርክተዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የቤኒሸኮ ዞን ኩራ ፈርዳ ወረዳ የሀገርን ህልውና እያረጋገጠ ለሚገኘው ሰራዊት ከ700 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም ፉሪ ሁለገብ የሴቶች ገበያ ማዕከል ከ61 ሴቶች የተሰበሰበ ከ7ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማበርከታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.