Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች በአፋር ክልል በጭፍራ ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው ወደ አገር ቤት የገቡ ዳያስፖራዎች በአፋር ክልል በጭፍራ ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ጎበኙ።
ሽብርተኛው ቡድን ወደ አፋር ክልል ዘልቆ ለመግባትና ሚሌን ለመቆጣጠር ባደረገው ሙከራ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ነው ዳያስፓራዎቹ ተዘዋውረው የጎበኙት።
ዳያስፖራዎቹ ባዩት ነገር እጅግ ማዘናቸውን እና የሽብር ቡድኑ ሀገር ለማፍረስ የሄደበት መንገድ አረመኔያዊነቱን በግልጽ እንደሚያሳይ ለፋና ገልፀዋል።
ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ የተመለከቱት የዳያስፖራ አባላቱ መልሶ ለማቋቋም ሰፊ ስራ እንደሚጠይቅ መመልከታቸውን ነው የተናገሩት።
የሽብር ቡድኑ በአካባቢው ሚሌን ለመቆጣጠር ያደረገው ሙከራ በወገን ጦር ከፍተኛ ተጋድሎ ህልም ሆኖበት እንደቀረ ይታወሳል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.