Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ በዘር ተሸፍኗል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል እስከአሁን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉም ተገልጿል፡፡

በክልሉ ግብርና ቢሮ አስተባባሪነትም ከዩኒቨርስቲዎች ፣ ከባለሀብቶችና ከምርምር ተቋማት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ÷ባለድርሻ አካላትም ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በቴክኖሎጂ፣ በእውቀትና በግብዓት አቅርቦት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ።

አርሶአደሩ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ጥቅምን ተረድቶ በዘላቂነት እስኪያመርት ድረስ በቴክኖሎጂና በአዳዲስ አሰራሮች የመደገፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለፁን ከክልሉ ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.