Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወሓት ቡድን የፈፀመውን ጉዳት የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በባህር ዳር ከተማ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች የፈፀመውን ጉዳት የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በባህር ዳር ከተማ ተከፈቷል።

አውደ ርዕዩን የዲያስፖራ አባላት እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲጎበኙት ለቀጣይ አምስት ቀናት ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል።

አውደ ርዕዩን የከፈቱት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ጀምበር፣ አሸባሪው የህወሓት ኃይል በአማራ ክልል በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ንጹሃን በጭካኔ በመግደል፣ አካል በማጉደል እና በማፈናቀል፣ መሰረተ ልማቶችን፣ ኢንዱስትሪዎችን እና የግለሰብ ሃብቶችን የቻለውን በመዝረፍ፣ ያልቻለውን በማውደም ከፍተኛ ጥፋት ፈፀሟል ብለዋል።

ይህን ሰብሠዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ለማሳየት ፎቶ ኤግዚቢሽኑ አስፈላጊ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

የአማራ ህዝብ ህልውናውን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ ውስጣዊ ክፍተቶችን በመሸፈን የሀሳብ እና የተግባር አንድነት በመፍጠር ፈተናዎችን መመከት እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.