በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ሰውና እንሰሳት እንዳይጎዱ በስፋት እየተሰራ ነው – የሶማሌ ክልል መንግሥት
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በተከሰተው ድርቅ በሰውና በእንሰሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለማድረግ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ የሶማሌ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡
የሶማሌ ክልል መንግሥት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በክልሉ አከባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ፥ ድርቁ በሰውና በእንስሳት ህይወት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ለዜጎች አስቸኳይ እርዳታ እያቀረበ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በሸበሌ ዞን ቤር-አኖ ወረዳ የሚገኙ የቆራህዳ፣ የገላ-መዶቦ ቀበሌ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የእንስሳት መኖ ማድረሱን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል።
በተጨማሪም የቤር-አኖ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ መሀመድ አብዱላሂ እንደተናገሩት ፥ በወረዳው ሥር የሚገኙ 15 ቀበሌ ነዋሪዎች የአስቸኳይ እርዳታ ከማድረጉ በተጨማሪ ከደናንና ከጎደይ ወረዳዎች እንዲሁም ከአጎራባቹ ኖጎብ ዞን ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችም የአስቸኳይ እርዳታ እየቀረበላቸው ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የድርቁ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ የዞኑን ነዋሪ ከድርቁ ለመታደግ፣ የሸበሌ ወንዝ ዳርቻን ለግብርና ልማት እንዲጠቀሙ ሰፊ የእርሻ መሬት እንደሚዘጋጅም አስተዳደሪው መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!