በቤጂንግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት እንደሚሰሩ ገለፁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤጂንግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የገናን በዓል በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ከኤርትራውያን ጋር በጋራ ባከበሩበት ወቅት እንደገለፁት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተመራው “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት”በአጭር ጊዜ ባስገኘው ድልና በመከላከያ ሰራዊቱ የተሰማቸውን ደስታና ኩራት ገልፀዋል።
ጦርነቱ ባስከተለው ጉዳት የወደሙ መሰረተ ልማቶችንና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በሙያቸውና በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ለማድረግ ተግተው እንደሚሰሩ ም ነው ያረጋገጡት።
በሕዝባዊት ቻይና ሪፕብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በስነስርአቱ ላይ እንደተናገሩት፥ የአሸባሪው ሀይል የጉዳት ሰለባዎችን ለመርዳት ሌት ተቀን ጥረት ሊደረግ ይገባል።
የምዕራባውያንንም ጫና ኢትዮጵያውያኑ በየተሰማሩበት የስራና የትምህርት መስኮች እውነተኛውን የሀገራቸውን ገፅታ በማንፀባረቅ ለመዋጋት ቀዳሚ የዜግነት ድርሻ በማድረግ መንቀሳቀስ ይገባልም ነው ያሉት።
በበአል አከባበሩ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ሰብሳቢ አቶ አስቻለው በላይ በበኩላቸው በታላቁ ወደ ሀገር ቤት የመመለስ እንቅስቃሴ ያላቸውን አጋርነትና የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ ያላቸውን ዝግጁነት በማህበረሰቡ ስም አረጋግጠዋል።
በበአል አከባበር ስነ ስርአት ላይ በቅርቡ ከተሰበሰበው አንድ ሚሊየን ብር በተጨማሪ በበዓሉ ምሽት ከተማሪዎች፣ በግል ስራ ከሚተዳደሩ ኢትዮጰያውያንና ከኤምባሲው ባልደረቦች 172 ሺህ ብር መሰብሰቡን የዝግጅት አስተባባሪ ዶ/ር ስንቅነሽ አጣለ ገልፀዋል።
በቻይና በተለያዩ ከተሞች በአብዛኛው ተማሪዎችን የሚወክሉና በግል ስራ ላይ የተሰማሩ ኡትዮጵያውያን እንደሚገኙ ከኤምባሲው የተገኝው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡