Fana: At a Speed of Life!

እኛ ኢትዮጵያውያን በአርቆ አስተዋይነት የፊታችንን በመገንባት የኢትዮጵያን ህልውና እናስቀጥላለን – አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እኛ ኢትዮጵያውያን በአርቆ አስተዋይነት የፊታችንን በመገንባት የኢትዮጵያን ህልውና እናስቀጥላለን ሲሉ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ፡፡
 
በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ÷ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተፈጸመውን ወረራ እና ግፍ በውጪ ለሚገኙ የሐይማኖት መሪዎች ማስረዳታቸውን በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል፡፡
 
በዚህ ወቅትም ምንም እንኳን ከሃያላን ሀገራት መጠነ ሰፊ ፖለቲካዊ ጫናዎች ቢደርሱብንም እኛ ኢትዮጵያውያን የሀገራችንን የነገ ዕጣ ፋንታ ለመወሰን ቃል ገብተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
አምባሳደሩ ÷ የፊታችንን ለማየት እና ነገን በመገንባት ኢትዮጵያን ለማስቀጠል የሚያስችል ጥበብ አለንም ነው ያሉት፡፡
 
አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከታዋቂ የሐይማኖት መሪዎች ጋር በበይነ መረብ ቆይታ በማድረጋቸው ክብር እንደተሰማቸውም ገልጸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.