ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር ለሚመጡ ዳያስፖራዎች ልዩ ማስተናገጃ ማዕከላት ተቋቁመዋል – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር ለሚመጡ ዳያስፖራዎች ልዩ የባንክ ማስተናገጃ ማዕከላትን ማቋቋሙን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጎንደር ዲስትሪክት አስታወቀ፡፡
ዲስትሪክቱ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ለሚፈልጉ ዳያስፖራዎች በነፍስ ወከፍ እስከ 30 ሚሊየን ብር የብድር አገልግሎት ማመቻቸቱም ተገልጿል።
የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ደሞዜ ባልቤ እንደተናገሩት፥ ባንኩ በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማው ለሚመጡ ዲያስፖራዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል።
ለዚህም ሦስት ልዩ የማስተናገጃ ማዕከላት ማቋቋሙንና ማዕከላቱም በቀን በአማካይ እስከ 500 የሚደርሱ ዳያስፖራዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን፥ ማዕከላቱም በጥምቀተ ባህሩ ግቢ፣ በአዘዞ አውሮፕልን ማረፊያ በዲስትሪክቱ ዋና መሥሪያ ቤት መቋቋማቸውን አስረድተዋል።
በጥምቀተ ባህር ግቢና በአዘዞ አውሮፕላን ማረፊያ የተቋቋሙት ማዕከላት የማንኛውንም ባንክ ካርድ ገንዘብ ለማውጣት የሚያስችሉ የኤ ቲ ኤምና የፖስ ማሽን እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት የሚሰጡ የገንዘብ መክፈያዎች እንደተከሉላቸው ገልጸዋል፡፡
ዲስትሪክቱ በጎንደር ከተማ ባሉት 22 ቅርንጫፎችም ለዳያስፖራዎች ተጨማሪ አገልግሎት እንደሚሰጡ ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!