በጦርነት ወቅት የደረሰውን የምጣኔ ሃብት ጉዳት ለመጠገን አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድገግ ይገባል
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነት ወቅት የደረሰውን የምጣኔ ሃብት ጉዳት ለመጠገን እና ዘርፉን ለማነቃቃት አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የምጣኔ ሃብት ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የዘርፉ መምህራንና ተመራማሪዎች፥ ጦርነት በተደረገባቸው ቀጠናዎች ሳይቀር ያሉ አማራጮችን በአግባቡ መጠቀም ይገባል ነው ያሉት፡፡
በሲቪል ሰርቪስ እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህርና ተመራማሪዎቹ ተባባሪ ፕሮፌሰር ካሳ ተሻገር እንዲሁም ዶክተር መኮንን ቦጋለ፥ የግብርናውን መስክ በተሻለ መደገፍ እና ለግል ባለሃብቱ ማበረታቻ በማድረግ ለኢኮኖሚው መነቃቃት መስራት ይገባል ብለዋል ፡፡
እንዲሁም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህሩ ከድር አብዱ፥ የግሉ ዘርፍ ሃገርን ከውድቀት ለመታደግ በሃገራዊ ሃላፊነት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል ፡፡
በአጠቃላይ የምጣኔ ሃብት ምሁራኑ፥ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ከሃገር ቤት ነባራዊ ሁኔታ የማቀናጀት የቤት ስራም ይጠበቃል ያሉ ሲሆን፥ ሃገራዊ የቤት ስራውን ስኬታማ ለማድረግ ደግሞ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ነው የገለፁት።
በአወል አበራ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!