Fana: At a Speed of Life!

በጋሸና ከተማ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በከፈተው ጦርነት ምክንያት በጋሸና ከተማ ለወራት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል::

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጋሸና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተገኝቶ ባደረገው ምልከታ አሸባሪው ቡድን ትምህርት ቤቱን ከህንጻው ውጭ ያሉ ንብረቶችን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን ተመልክቷል።

ከዘረፋው እና ከውድመቱ በተጨማሪም በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ በመማሪያ ክፍሎች አቅራቢያ በአሸባሪው ቡድን የተፈጸሙ ጅምላ መቃብሮች ትምህርት ለመጀመር ፈተና እንደሆነበት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ዮናስ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ተማሪዎች ያለትምህርት እንዳይቀመጡ በማሰብ ትምህርት ቤቱ በተዘረፉ እና በወደሙ ቁሳቁሶች ምትክ ሊያገለግሉ የሚችሉ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ እንዲሁም የአከባቢውን ነዋሪ በማስተባበር ወደ ስራ ለመግባት እየጣረ መሆኑን አመልክተዋል።

መምህራንም በግል የያዟቸውን የተማሪዎች መረጃዎችን በጋራ በመሰብሰብ እየሰነዱ እንደሚገኙ ነው የጠቆሙት።

የአካባቢው ማህበረስብም ሆነ ሌሎች አካላት ትምህርት ቤቱን በተሻለ ደረጃ ወደ ስራ ለማስገባት ድጋፍ እንዲያደርጉ ርእሰ መምህሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በለይኩን ዓለም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.