Fana: At a Speed of Life!

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሁሉም ክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊዎች ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሁሉም ክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

በዋናነትም የኢትዮጵያ ኢነርጂ ፖሊሲ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

ከየክልሉ አመራሮች የሚገኙ ገንቢ ሀሳቦች ተካተው ለፖሊሲው ግብዓት ይሆናሉ የተባለ ሲሆን፥ በተጨማሪም ከታዳሽ ኃይል ጋር ተያይዞ ምን መሰራት አለበት የሚለውም ለውይይት ይቀርቧል፡፡

እንዲሁም ክልሎች በዘርፋ የሠሩትን ሥራ እና የገጠሙ ተግዳሮቶች እና በ2025 የኢትዮጵያን የኤሌትሪክ ኃይል የማዳረስ እቅድ ላይም ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሐብታሙ ኢተፋ፥ ኢትዮጵያን መለወጥና የኢትዮጵያን እናቶች መጥቀም ካስፈለገ በዘርፉ ያሉ አካላት ታዳሽ ኃይልን ማስፋፋት እንደሚገባ ገልፀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

 

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.