የዳያስፖራ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ አላማውን ያሳካ ነው – ዳያስፖራ ኤጀንሲ
አዲስ አበበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ አላማውን ያሳካ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ገለጸ፡፡
የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የአሁኑ ጉዞ ለሀገራቸው የበለጠ መስራት እንዳለባቸው የተገነዘቡበት እንደሆነ ገልጸዋል።
ከሀገር ቢወጡም ሀገር ግን ከልባቸው እንደማትወጣ ከካናዳ የመጡት ዶክተር ገዛሃኝ ሆርዶፋ ተናግረዋል፡፡
በታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ ኢትዮጵያን በተለያዩ ስፍራዎች ተዘዋውረው ነባራዊ ሁኔታዎችን እንደተረዱ ገልጸው፥ ስንተባበር የሚያቅተን ነገር የለም ብለዋል፡፡
ወጣቷ ዳያስፖራ ሀወኒ ዓለሙም በዚሁ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ መምጣቷን ነው የገለጸችው፡፡
ወደተለያዩ አካባቢዎች ከጓደኞቿ ጋር ተዘዋውራ እውነታውን መረዳቷንና መረጃዎችንም መሰብሰቧን ነው የተናገረችው፡፡
በአካል የተመለከቷቸውን እውነቶች፣ የሰበሰቧቸውን መረጃዎችም ወደ ሀገር ቤት ላልመጡ ዳያስፖራዎችና ለዓለም ለማጋራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ልምድና እውቀት ያላቸው መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ ቱሪዝምና ሆቴል ማርኬተር ማህበር ሊቀመንበር ጌታሁን ዓለሙ፥ ይሄንን እውቀት ለሀገር ግንባታ ለመጠቀም የሚያስችሉ ስልቶችና አሰራሮች መተግበር እንዳለባቸው ይመክራሉ፡፡
ለዚህም ይረዳ ዘንድ አሰራሮችን ከዘመቻ ወደ ተቋም መቀየር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በዚህም ታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ በልዩ ልዩ መመዘኛዎች የተያዘለትን ግብ ያሳካ ስለመሆኑ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ እንድሪስ ያነሳሉ፡፡
የዳያስፖራው መምጣት ሀገራዊ አንድነትንና ወዳጅነትን ያዳበረ፣ በመንግስትና በዳያስፖራው መካከል መቀራረብን የፈጠረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!