Fana: At a Speed of Life!

የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13 ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13 ቀን 2014ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ የሚታወስ ሲሆን÷ በዚሁ መሠረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ከታህሳስ 26 እስከ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

እስካሁን ዕጩ ኮሚሽነሮችን ለመጠቆም ዜጎች ያሳዩት ተነሳሽነትና እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ የሚያበረታታ ነው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

ይሁንና ኮሚሽኑ ከሚኖረው ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት አንፃር ተጨማሪ ዕጩዎችን ህዝቡ እንዲጠቁም እንዲሁም የአገሪቱን ብዝሃነት ታሳቢ በማድረግና በተለያዩ ምክንያቶች መጠቆም ላልቻሉ ዜጎች ዕድሉን ለመስጠት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.