የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ድጋፍ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት /IOM/የድንበር አስተዳደር ስራን ለማጠናከር የሚያስችል ድጋፍ አገኘ።
የአለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት የኢፌዲሪ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአገሪቱን የድንበር አስተዳደርን ስራ ለማሻሻል እያሰራ ያለውን ስራ ለማገዝና ለማጠናከር የሚያስችል ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያለባቸውን የየብስ ኬላዎችን ለማጠናከር ሶስት ደብል ካፕ ላንድ ክሩዘር ቲዮታ መኪኖች፣ 24 ሞተር ሳይክሎች፣ አንድ ሳኒታይዚንግ ታነል ማሽን እና በቀጣይ ለሚከፈቱ በርካታ ኬላዎች ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች በዛሬዉ እለት ለኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት አስረክቧል።
በርክክብ ሂደቱ የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጅብ ጀማል እንደገለጹት IOM ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል።
በዛሬዉ እለት ከጀርመን መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ያገኘው ድጋፍ በድንበር አካባቢ የሚያከናውናቸዉን በርካታ የቁጥጥር ስራዎች ከማገዝ እና የኬላዎችን አቅም ከማጠናከር አንጻር የጎላ አስተዋታጽኦ እንደሚያበረክት መጠቀሱን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!