Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌደሬሽን በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ፍራሲስኮ ሮካ በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡

በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ ከዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌደሬሽን እንዲሁም ከጣሊያን ቀይ መስቀል ፕሬዚዳንት ፍራሲስኮ ሮካ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ደሚቱ  በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ  እና አሸባሪው ህወሓት  በወረራ ይዟቸው በነበሩ የአማራና አፋር  ክልሎች በርካታ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎችን ማውደሙን አብራርተዋል፡፡

ፌደሬሽኑ  በኢትዮጵያ እስካሁን ወጥነት በተሞላበት ሁኔታ ሲያደርግ የቆየውን  ድጋፍ አድንቀው፥ በቀጣይም  በሽብር ቡድኑ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ድጋፉን  አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡፡

ፍራሲስኮ ሮካ በበኩላቸው  በኢትዮጵያ እየተካሄዱ የሚገኙ ለውጦችን በቅርበት እንደሚከታተሉ ገልጸው፥ ለህክምና ተቋማት የሚያስፈልጉ አስቸኳይ ግብዓቶችን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.