Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቋቋም እንዲቻል በአጭር ጊዜ እቅድ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለፀ።

ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በሁለቱ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ በእንሰሳት ላይ ጉዳት አድርሷል።

በተለይ ቆላማ በሆኑ በቦረና፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅና ምእራብ ሐረርጌ እንዲሁም ሶማሌ ክልል አካባቢዎች ድርቁ ባስከተለው ጉዳት ችግር እያጋጠመ መሆኑን አመልክተዋል።

በመሆኑም መንግሥት አፋጣኝ ርምጃ በመውሰድ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀው፥ ቁፋሯቸው ከተጠናቀቁ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ውሃ በማውጣት በቦቴ በማመላለስ የእንስሳት ሀብቱን የመታደግ ስራ እየተከናወነ ነው።

በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በርካታ የቤት እንሰሳት መጎዳታቸውን ገልጸው፥ መንግሥት በአሁኑ ወቅት ጊዜያዊ የመፍትሄ ርምጃዎችን መውሰዱን ገልፀዋል። ከዚህም ባሻገር በአጭርና በመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ ኅብረተሰቡ በዝናብ ወቅት ከቤቶች ጣራ ላይ የሚወርደውን የዝናብ ውሃ በማጠራቀም እንዲጠቀም ከ700 ሺህ በላይ ዜጎችን ተደራሽ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ትግበራ ተገብቷል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.