ሀገርን በጠንካራ አለት ላይ ለማቆም የምክክር ኮሚሽኑ አስፈላጊ ነው – የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይነት የማይናወጥ የሰላም ሁኔታ ውስጥ ለመግባትና ሀገርን በጠንካራ አለት ላይ ለማቆም ሀገራዊው የምክክር ኮሚሽኑ አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ አቶ ዘላለም ግዛቸው ከፋና ብሮድካስቲንግ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በየጊዜው በምክክር ነገሮችን ከማለፍና የህዝብን መሰረታዊ ፍላጎትና መሻት መሰረት አድርጎ ፖለቲካውን ከመዘወር ይልቅ በግል ፍላጎት ላይ መንተራሱ ብዙ የቤት ስራዎች እንዲከማቹ እንዳደረገው ይናገራሉ፡፡
እንዲሁም ባለፉት ጊዚያት የመጣንባቸው የተሳሳቱ አካሄዶች፣ የሀሰት ትርክቶችና የተሳሳተ ፖለቲካ በዚህኛው ትውልድ ጦርነት እንዲከሰት አድርጓል ባይ ናቸው።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በበርካታ የልዩነት ምክንያት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብሄራዊ መግባባትን በመፍጠር አሁን ከገጠመን የጦርነት አዙሪት ብሎም የኛን ድጋፍ ካልሰጠናችሁ ከዚህ ችግር መውጣት አትችሉም በሚል የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም ለማተራመስ የሚፈልጉትንም ስርዓት ሊያሲዝ የሚችል መሆኑም ተገልጿል፡፡
የምክክር ኮሚሽኑ ከአሁናዊ ችግሮች ባለፈ በቀጣይነት የማይናወጥ የሰላም ሁኔታ ውስጥ ለመግባትና ሀገርን በጠንካራ አለት ላይ ለማቆም አስፈላጊ ስለመሆኑ ነው ባለሙያው ያነሱት፡፡
ለውጤታማነቱ ሁሉም ድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡
በታሪኩ ለገሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!