Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር የሚከበረው የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፀጥታ ስራ እየተከናወነ ነው – ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በሰለም እንዲከበር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፀጥታ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የጥምቀት በዓል በዩኒስኮ ከማይዳሰሱ ቅርሶቹ መካከል አንዱ ሲሆን ፥ ይህ በዓል በጎንደር ከተማ በሰላም እንዲከበር በየአካባቢው የጥበቃ ሁኔታና የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተጠቁሟል።

ለዚህም ህብረተሰቡን ያሳተፉ አደረጃጀቶችን ፈጥሮ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የጎንደር ከተማ መደበኛ ፖሊስ፣ የአድማ መከላከል ፖሊስ፣ ሚሊሻና የግል ታጣቂዎች የብሎክ አደረጃጀቶችን በሰረት በማድረግ አካባቢውን የመጠበቅ ተግባር እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከመቸውም ጊዜ በላይ አካባቢያቸውን እንዲጠብቁና ሁሉም ህብረተሰብ “የከተማዋ ሰላም የኔ ሰላም ነው” ብሎ የድርሻውን እንዲወጣ የጎንደር ከተማ ፖሊስ ጥሪ ማቅረቡን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.