በርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ የተመራ ልዑክ የመስኖ ስንዴ ማሳን እየጎበኘ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በጋሞና ወላይታ ዞኖች እየተካሄደ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እየጎበኘ ነው።
በጉብኝት መርሃ ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ እና የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ አመራሮችና የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
አሁን ላይ ልዑኩ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በጋሞ ልማት ማህበር አባያ ሐይቅ አካባቢ የለማ የስንዴ ሰብል እየተጎበኘ መሆኑን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በደቡብ ክልል በያዝነው የበጋ ወቅት በተለያዩ ዞኖች ከ11 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መስኖን በመጠቀም የቆላ ስንዴ መልማቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።