Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ አትሌቶች እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ አትሌቶች እውቅና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ፌዴሬሽኑ በጉባኤው በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ አትሌቶችን እውቅና የሰጠ ሲሆን፤ በጦር ግንባር ዘመቻው ለተሳተፉት አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ ኮማንደር ማርቆስ ገነቴ ፣ ዋና ኦፈሰር ፋንቱ ሚጌሶ፤ ሻለቃ ሐይሌ ገብረስላሴና ፈይሳ ሌሊሳ እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

በጉባዔው የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉና የጉባኤው አባላት ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ኮለኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የመግቢያ ንግግር ማድረጋቸውንም ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.