Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች 88 ሺህ የካናዳ ዶላር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች 88 ሺህ የካናዳ ዶላር ድጋፍ አደረጉ፡፡

 

የኢትናስ አመራሮች ድጋፉን በአፋር ክልል ቡሰዲሚ በተባለ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ በመገኘት ለአፋር ክልል መንግስት ማስረከባቸውን የኢክናስ የቶሮንቶ ቻፕተር አባል ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተ/ሚካኤል ለኢዜአ ገልፀዋል፡፡

 

የ88 ሺህ የካናዳ ዶላር ድጋፉን ያደረጉት የኢትናስ፣ የቶሮንቶ፣ ሃምሊተንና ኤድመንተን ቅርንጫፎች መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

 

ጋዜጠኛ ብርሃኑ ፥ ኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ (ኢትናስ) ከዚህ ቀደም በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የ50 ሺህ የካናዳ ዶላር ድጋፍ ማድረጉን  አስታውሰዋል፡፡

 

ድርጅቱ ከተቋቋመበት ህዳር ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለወቅታዊ አገራዊ ጥሪ እና የልማት ፕሮጀክቶች 5 ሚሊየን የሚጠጋ የካናዳ ዶላር በገንዘብና በአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.