የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ ከ72 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች በተደረገ ለተፈናቀሉ ወገኖች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከ72 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፥ “ኮቪድ 19፣ በረዶም ሆነ ብርድ ወገንን ለመርዳት አያግድም” በሚል ጥቂት ሆናችሁ እንደ ብዙ፣ ከ72 ሺህ በላይ ስላሰባሰባችሁ እናመሰግናለን’’ ብለዋል፡፡
እንዲሁም በሰሜን ካሮሊና ስቴት ዩኒቨርሲቲ ስለነበራቸው የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ኢኖቬሽን ውይይት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በወጣቶች የተገነባው ግብረ ኃይል በአጭር ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ድጋፍ በማሰባሰብ ለሌሎች አርአያ መሆኑንም አምባሳደር ፍፁም ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!