የሀረሪ ክልል በድርቅ ለተጎዱ የሶማሌ ክልል አካባቢዎች የሚሆን የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የሀይማኖት አባቶች ያካተተ ልዑክ ዛሬ ጂግጂጋ ገብቷል፡፡
ልዑኩ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የ10 ሚሊየን ብር እና የ1 ሚሊየን ብር የዓይነት ድጋፍ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ አስረክቧል፡፡
ድጋፉንም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ተረክበዋል፡፡
ሁለቱ ክልሎች በታሪክና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን የገለጹት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ÷ አሁንም ወገን ለወገን ደራሽነትን በተግባር እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡
ድርቁ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ርብርብ እየተደረገ ባለበት ሰዓት ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፡፡
መረዳዳትና መተጋገዝ የሁለቱ ወንድም ህዝቦች የነበረ እሴት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የሁለቱ ክልል ህዝቦች ከእንደዚህ አይነት ተግባር በተጨማሪ በምስራቁ ክፍል ባለው በጸጥታና ደህንነት ዙሪያ በጋራ እንሰራለንም ብለዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ እና ጌታሰው የሽዋስ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!