Fana: At a Speed of Life!

የከተራና የጥምቀት በዓል ተሳታፊዎች በዓሉን ሲያከብሩ ርቀታቸውን በመጠበቅና ከንክኪ በመቆጠብ ሊሆን እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ጥር 9፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተራና የጥምቀት በዓል ተሳታፊዎች በዓሉን ሲያከብሩ ርቀታቸውን በመጠበቅ ፣ ከንክኪ በመቆጠብ ፣ በተደጋጋሚ እጃቸውን በማጽዳት እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ሳያወልቁ በመንቀሳቀስ ሊሆን እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
ሚኒስቴሩ ለክርስትና እምነት ተከታዮች፥ ለከተራና ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ሚኒስቴሩ በመልዕክቱ÷ የከተራና የጥምቀት በዓል በምዕመናን በብዛት የሚታጀብና አካላዊ ንክኪው እና ጥግግቱ የጠነከረ በመሆኑ ሰዎች ስሜቶቻቸውን ስገልጹ በጥንቃቄ ሊሆን እንደሚገባ ነው ያሳሰበው።
ይህ ሁኔታ በተለይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከሰው ወደ ሰው በማስተላለፍ ረገድ ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር ስለሚችል፥ በዓሉን ለማክበር የሚሰባሰቡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡
የበዓሉ ተሳታፊ ምዕመናንም በተቻለ መጠን ርቀታቸውን በመጠበቅ ከንክኪ በመቆጠብና በተደጋጋሚ እጃቸውን በማጽዳት እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ሳያወልቁ በመንቀሳቀስ በዓሉን ማክበር እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.