ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ንጹሃን ላይ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አሸባሪዎች መኖሪያ አካባቢዎችን ዒላማ በማድረግ የፈፀሙትን ጥቃት አወገዙ።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፥ ድርጊቱን ኮንኖ በዓለም አቀፍ ህግም ሆነ በሰብአዊነት ፈጽሞ ይሄ ነው ሊባል የሚችል ምክንያት የማይቀርብለት የፈሪዎች ተግባር ነውም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብም ጥቃቱ ለተፈጸመባቸው የተሰማቸውን ልባዊ ሃዘን ይገለፃሉ ያለው መግለጫው፥ መጽናናትን ለቤተሰቦቻቸው ይመኛሉ ነው ያለው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሃዘን መግለጫው፥ ኢትዮጵያ በእንዲህ ያሉ ወቅቶችም ከተባበሩት አረብ ኤምሬት መንግስትና ሕዝብ ጋር በአብሮነት ለመቆም ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ታረጋግጣለች ብሏል፡፡