በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የመድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በመጪው ሰኞ አገልግሎት ይጀምራል
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪውና ወራሪው የህወሓት ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ደሴ ቅርንጫፍ ከሰኞ ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡
ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በለይ የሚገመት ንብረት በወራሪው ቡድን የወደመበት ተቋሙ ፥ በአማራ ክልል ለ58 ፤ በአፋር ክልል ለሁለት ወረዳዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
የኤጀንሲው ስራ አስኪያጅ አቶ እሸቴ ሹሜ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷ በሀገር ደረጃ የሚገኙት 17 የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲዎች እና የፌደራል ተቋማት ባደረጉት ሁለንተናዊ ድጋፍ ከፊታችን ሰኞ 16 ቀን 2014 ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት ማቅረብ እንጀምራለን ብለዋል።
የቅርንጫፍ ኤጀንሲው ሰራተኞች ቁርጠኝነት፣ ፈቃደኝነት እና የተደረገው እገዛ በፍጥነት ወደ ስራ እንድንገባ አድርጎናል ያሉት ስራ አስኪያጁ፥ ለተባባሪዎች ሁሉ ምስጋናም አቅርበዋል።
በእሸቱ ወ/ሚካኤል
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!