የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ማቅረቢያ ዛሬ ይጠናቀቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ዛሬ ጥር 13/2014 ዓ/ም እንደሚጠናቀቅ ጥቆማ ተቀባይ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸውና የሀገራችንን ህልውና የሚፈታተኑ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ ለመጪው ትውልድ ሰላማዊ ሀገር ለማስረከብ የሚያግዝና ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለልተኛ የሆነ ኮሚሽን እንደሚቋቋም ይታወቃል፡፡
ይህንን ኮሚሽን የሚመሩት ኮሚሽነሮች በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥቆማ ተቀባይነት ከታህሳስ 26/2014 እስከ ጥር 13/2014 ዓ.ም ድረስ ህዝቡ በተለያዩ አማራጮች ጥቆማ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ዛሬ ጥር 13/2ዐ14 ዓ/ም የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ የመጨረሻ ቀን በመሆኑ እስካሁን ጥቆማ መስጠት ያልቻላችሁ ዛሬ ጥር 13/2014 ዓ/ም ጥቆማ መስጠት የምትችሉ መሆኑን የጥቆማ ተቀባይ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
“እንደ ዜጋ በሃገራዊ ጉዳይ ላይ የመወሰን መብትን በመጠቀም ጥቆማውን እንድታደርጉ” በማለት በምክር ቤቱ የተቋቋመው የጥቆማ ተቀባይ ኮሚቴ ጥሪውን አቅርቧል ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!