Fana: At a Speed of Life!

የግዮን በዓል በሰከላ ወረዳ በድምቀት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ ወንዝ አባይ መነሻ በሆነው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ሰከላ ወረዳ የግዮንና የጻዲቁ ዘረያዕቆብ አመታዊ ክብረበዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
 
በበዓሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃለ ከፋለን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
 
በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰከላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ አድማስ÷ የታላቁ አባይ መነሻ የሆነው የጊዮንና የጻድቁ ዘረያቆብ በዓለ ጥምቀት መከበር የጀመረው ከአራት አመት በፊት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
 
በየአመቱ ጥር 13 ቀን የሚከናወነው ይህ በዓል መንፈሳዊና ታሪካዊ ይዘት እንዳለውም ነው ያወሱት።
 
የተዳሚውም ቁጥር እየጨመረ መሆኑን በመጥቀስ ይህ ታሪካዊና መንፈሳዊ በዓል የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን በወረዳው በኩል ጥረት እተደረገ ይገኛል ብለዋል።
 
መንግሥት የወረዳውን የልማት ጥያቄ ምላሽ እየሰጠ መሆኑና ከዚህ ውስጥም የመንገድ ልማት እንደሚገኝበትና ይህም መንፈሳዊና ታሪካዊ ይዘት ያለውን የቱሪስ መዳረሻ ለማድረግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ያግዛል ነው ያሉት።
 
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ በበኩላቸው ዐባይ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፣ ቅርስ፣ ልማት መሆኑን በማስታወስ፣ ይህን ውድ የሆነ ሀብት ማሳደግና ማልማት ስፍራው ንም የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ ከአጽናፍ አጽናፍ በዓለም እንዲጎበኝ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
 
የክልሉ መንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት።
ርዕሰ መስተዳድሩ ታሪኩን በመጠበቅ አሁን ላይ ላደረሰችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምስጋና ማቅረባቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
 
ወረዳዋ የዓባይ ወንዝ መነሻ የግሼ ተራራ፣ የፋሲል ግንብ (ፋሲል ጎንደር ከመግባቱ በፊት የገነባው)፣ የጉደራ ሐይቅ፣ የዓላዛር ዋሻ ፣ ድንጋይ ቀዳዳ እና የሌሎች የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ባለቤት በመሆኗ ወረዳዋን ለማስተዋወቅ በዓሉ መከበሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ተብሏል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.