በደቡብ ወሎ ዞን የህወሃት ቡድን ከ217 በላይ ሴቶችን መድፈሩ በዳሰሳ ጥናት ተረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውና ወራሪው የህወሃት ቡድን ከ217 በላይ ሴቶችን መድፈሩ በመጀመሪያ የዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡን የደቡብ ወሎ ዞን አሰተዳደር አስታወቀ።
የዞኑ አሰተዳዳሪ ዶክተር አብዲ ሁሴን እንደተናገሩት ፥ በመጀመሪያ ዙር የዳሰሳ ጥናት አሸባሪው ቡድን አካባቢውን በወረረበት ወቅት ከ217 በላይ ሴቶች መድፈሩን አስታውቀዋል።
የጥቃቱ ሰለባዎችም ከ8 ዓመት እድሜ ጀምሮ እስከ አረጋውያን ሴቶች መሆናቸውንም ነው ያብራሩት።
ቡድኑ ከ548 በላይ ንጹሃንን መግደሉን በጥናቱ ደርሰንበታል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ፥ በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
ጥናቱ የመጀመሪያ ዙር መሆኑን የገለጹት አሰተዳዳሪው፥ በቀጣይ በሚገኘው ግኝት ቁጥሮቹ ሊጨምሩ እንደሚችል ጠቁመዋል።
በከድር መሀመድ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!