Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ መሰረታዊ መድሃኒቶችን ለትግራይ ክልል በዓየር ማድርሱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ መሰረታዊ መድሃኒቶችን ለትግራይ ክልል በዓየር ማድርሱን ገለፀ።

ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ወደ መቀሌ በአየር የተጓጓዙት መድሃኒቶች በክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት እንደሚሰራጩ ነው ያስታወቀው።

እስካሁን የተላኩት መድሃኒቶች ለሆስፒታሎች እየደረሱ መሆኑን የጠቆመው ማህበሩ፥ በቀጣይ ቀናቶች እና ሳምንታት አስፈላጊ መድሃኒቶችን ወደ ክልሉ በዓየር ለማጓጓዝ እንደሚያመቻች ነው ያመለከተው።

ድርጅቱ በጦሩነቱ ክፉኛ የተጎዱ በአማራ እና አፋር ክልሎች ለሚገኙ የጤና ተቋማትም ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.