በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የእንሰሳት መኖ በድርቅ ለተጎዱ የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ግምቱ 5 ሚሊዮን ብር የሆነ የእንሰሳት መኖ በድርቅ ለተጎዱ የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ድጋፍ አደረገ።
የእንስሳት መኖ ድጋፉ ከዞኑ አርሶ አደሮች የተሰባሰበ መሆኑን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደአማኑኤል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
“ለክልሎቹ ያለንን አጋርነት ለማሳየት ነው የመኖ ድጋፉን ያደረግነው” ያሉት አቶ ሲሳይ፥ በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሃት የተፈጸመውን ወረራ የቀለበስነው በአንድነት ነው አሁንም በክልሎቹ ድርቅ ያደረሰውን የመኖ ዕጥረት በጋራ በመረዳዳት እናልፈዋለን ብለዋል።
ዞኑ ከየ ወረዳዎቹ ያሰባሰበውን ከ1 ሺህ ቶን በላይ የእንሰሳ መኖን ወደ ሶማሌ ክልልና ኦሮሚያ ቦረና ዞን ማጓጓዝ የጀመረ ሲሆን፥ በቀጣይም መሰል ድጋፎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል።
በአላዩ ገረመው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!