Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔና በ40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

ዛሬም የአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳሳደር ራምታን ላማምራ አዲሰ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቢኔ ጉዳዮች ዋና ሹም አምባሳደር ምህረተዓብ ሙሉጌታ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና በ40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ እስካሁን የሶማሊያ፣ ካሜሩን፣ ቻድ፣ ኮትዲቯር፣ ኮንጎ፣ አንጎላ፣ ጅቡቲ፣ ሊቢያ፣ ሞሪታኒያ፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኒጀርና አልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.