Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን የፈረንሳይ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የፈረንሳይን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን ክቡር አምባሳደር ፍሬድሪክ ክላቬዬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ የፈረንሳይ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ረዥም ጊዜን ያስቆጠረ መሆኑን አውስተው፥ በቀጣይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጥ ለማጠናከር በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት መኖሩን አስረድተዋል፡፡

የፈረንሳይ መንግስት የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ መመልከቱም የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተም ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ መምጣታቸውን፣ መንግስት ለሰላም ሲል በቅርቡ እስረኞችን መፍታቱን፣ ብሔራዊ መግባባትን ያለመ ሁሉን አቀፍ ውይይት ለማድረግ እየተሰራበት መሆኑን አብራርተዋል።

እንዲሁም በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና ሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል፡፡

በመንግስት በኩል ሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽ ለማድረግ ቁርጠኝነት ያለ ቢሆንም፥ የህወሃት የሽብር ቡድን በአጎራባች የአማራ እና የአፋር ክልሎች እያደረሰ ባለው አዲስ ጥቃት ምክንያት እክል እየፈጠረ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

የፈረንሳይ ልዩ መልዕክተኛው ክቡር አምባሳደር ፍሬድሪክ ክላቬዬ በበኩላቸው፥ ለተደረገላቸው ማብራሪያና ገለጻ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ኢትየጵያ በአካባቢው ጠንካራ እና ተጽእኖ ፈጣሪ አገር መሆኗን ልዩ መልዕክተኛው ጠቅሰው፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለመጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትየጵያ መንግስት በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ለሚያደርገው ጥረት የፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር ለማካሄድ ለሚደረገው ውይይትም መንግስታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ልዩ መልዕክተኛው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.