በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተመራ ልኡክ ጅግጅጋ ከተማ ገባ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተመራ ልኡክ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ጅግጅጋ ከተማ ገባ።
የልኡካን ቡድኑ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልኡኩ ወደ ስፍራው ያቀናው በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መሆኑን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአማራ ክልል፤ በኦሮሚያ ክልል ጎጂና ቦረና አካባቢዎች በድርቅ ለደረሰው ጉዳት በትናንትናው እለት የእንስሳት መኖ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡