በሰሜን ሸዋ ዞን በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ23 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን የልማት ኮሚሽን በሰሜን ሸዋ ዞን በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 23 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አድርጓል።
ኮሚሽኑ በዞኑ መሐል ሜዳ ከተማ በመገኘት በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸውና ተፈናቅለው ለነበሩ ከ22 ሺህ በላይ ወገኖች ነው የዕለት የምግብ ድጋፍ ያደረገው።
የልማት ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ታሎሬ ÷ የተደረገው ድጋፉ ግምታቸው 23 ሚሊየን ብር የሆነ የስንዴ ዱቄት፣ ባቄላ፣ ዘይትና አልሚ ምግቦችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የልማት ኮሚሽኑ በቀጣይም በማቋቋም ስራው ላይ የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ ዶክተር ተፈራ ተናግረዋል።
በግርማ ነሲቡ