ቀጠናዊ ትስስር ለበለፀገች አፍሪካ
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካን በአጀንዳ 2063 የበለፀገች አህጉር ለማድረግ ህብረቱ ከያዛቸዉ ሰባት ውጥኖች ውስጥ በፖለቲካዊ አንድነትና በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎች በአፍሪካ ህዳሴ ላይ የተመሰረተ የተቀናጀ አህጉርን መፍጠር አንዱ ነዉ።
መሰል እሳቤዎች ከሚገለጡባቸው ተግባራት መካከል ደግሞ የሀገራት ግንኙነትን የሚያሳልጡበት የድንበር ላይ አገልግሎቶች ተጠቃሾች ናቸው።
በኬንያ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ዳይሬክተርና የአንድ ቋት “የአንድ አለቅ” አገልግሎት ባለሙያው ዶክተር ዋሁንጉ ፥ የአንድ አለቅ የድንበር አገልግሎቱ በእያንዳንዱ ሰዉ የሚመነዘር ጥቅም አለው ይላሉ ፡፡
ሀሳቡም ከታሪክ እንደምንረዳው አፍሪካ ይህ እንዲሆን ፍላጎት አላት፤ አሁን የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናም የተለያዩ “የአንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት”ን እየተገበረ ነው ‘’ ብለዋል፡፡
ሀገራት በዘረጓቸው የመሰረተ ልማት አውታሮች የንግድ ግንኙነትን ማከናወን ከቻሉ፥ ለነፃ የንግድ ስምምነት ትግበራውና አህጉረ አፍሪካን በንግድ ለማስተሳሰር የሚከናወነውን ስራ ቀላል የሚያደርግ ነው የሚሆነው፡፡
ዶክተር ዋሁንጉ እንደሚሉት÷ የሞያሌ “የአንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት” በሀገራት ግንኙነት የአፍሪካን የእርስ በእርስ ትስስሯን ያጠናክረዋል ፡፡
ከዚህ ባለፈም “ይህ አገልግሎት የድንበር ላይ ቅልጥፍናንም ይጨምራል ፤ የድንበር ላይ አገልግሎቶቻችን የተሻሉ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ ይሆናሉ ፣ ቀጣናችን እንዲለማና እንዲበለጽግ አቅም ይሆናሉ” ሲሉ ያብራራሉ፡፡
ነገር ግን የአፍሪካን መልማት የብሔራዊ ጥቅማቸው ስጋት አድርገው የሚያዩ አንዳንድ ምዕራባውያን እና የዉጭ ኃይላት አፍሪካ በራሷ እንዳትቆም እጅ የመጠምዘዝ ሙከራ ሊያደርጉ ይችላሉ።
ዶክተር ዋሁንጉ ፥ ቃጠናዊ ትስስር በውጭ ኃይላት ተፅእኖ ውስጥ እንዳይወድቅ ምን እናድርግ የሚለው ስጋት ሊያሳስብ አይገባም ይላሉ።
ምክንያቱም ትስስርን የመፍጠር ጥቅምን ጠንቅቀን እንረዳለንና በመሰል የውጭ ኃይላት ጣልቃ ገብነት የአፍሪካ ሀገራት በመተሳሰር የመለወጥ መንገድ አይደናቀፍም ብለዋል ባለሙያው።
“የአንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት” ለጠነከረችና ለበለጸገች አፍሪካ የመጀመሪያው እርምጃ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ዋሁንጉ፥ የዘርፉ ፋይዳ ከፍ ያለ በመሆኑ በአፍሪካ ቅድሚያ የሚሰጠውና ሊሰጠው የሚገባ የኢኮኖሚ ትስስርን የሚያሳድግ ነው ብለዋል፡፡
በፀጋዬ ወንድወሰን
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!