Fana: At a Speed of Life!

የሀገረመቆር-ቁንዲ ክፍል ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም 90 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገረመቆር- ቁንዲ ክፍል ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም 90 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በተያዘው በጀት አመትም ዋና ዋና ስራዎቹን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

102 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ይህ መንገድ 81 ኪሎ ሜትር የሚሆን የአስፓልት ንጣፍ ስራው የተጠናቀቀለት ሲሆን፥ ቀሪ ዋና ዋና ስራዎችን ጨምሮ የማጠቃለያ ስራዎችን ለመፈጸም በትኩረት እየተሰራ ነው ተብሏል ።

ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ዓለም-አቀፉ የስራ ተቋራጭ ቻይና ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ድርጅት መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፥ መንገዱን ለመገንባት የሚስፈልገውን 1 ቢሊየን 558 ሚሊየን ብር በኢትዮጵያ መንግስት እየተሸፈነ መሆኑን ገልጿል፡፡

የማማከሩን እና የቁጥጥሩን ስራ ደግሞ ስታዲያ ኢንጅነሪንግ ከጂ እና ዋይ ኢንጅነሪንግ ጋር በጥምረት እያከናወኑት ይገኛሉ፡፡

መንገዱ ሲጠናቀቀም ከዚህ ቀደም መንገዱ ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ምቹ ባለመሆኑ የሚፈጥረውን እንግልት ያስቀራል እንዲሁም በአካባቢዉ የሚገኙትን ከፍተኛ የቁም እንስሳት እና የእንስሳት ተዋፅዖ ምርቶችን በፍጥነት ወደገበያ ለማድረስ ያግዛል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.