Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ራማታን ጋር ተወያይተዋል።
 
በወቅቱም አቶ ደመቀ መኮንን የአልጀሪያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት የቆየ መሆኑን በማንሳት፥ በቀጣይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት መኖሩን አንስተዋል፡፡
 
በተጨማሪም የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታም በተመለከተ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉን አቀፍ ውይይት ለማድረግ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቋቋም የአባላት ምርጫ እየተካሄደ መሆኑን፣ እንዲሁም የአገራችን የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፉን፣ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትን ለማሳደግ ጥረት እተደረገ መሆኑን አቶ ደመቀ ገልጸዋል፡፡
 
በመንግስት በኩል ሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽ ለማድረግ ቁርጠኝነት ያለ ቢሆንም የህወሃት የሽብር ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች እያደረሰ ባለው አዲስ ጥቃት እክል መፍጠሩንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
 
የአልጀሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ከአገራችን ጋር ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ለማሳደግ በተለይም በአየር በረራ አገልግሎት ዙሪያ ለመተባበርና በቀጠናዊና አህጉራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ ትብብሮችን ለማጠናከር በሀገራቸው በኩል ፍላጎት መኖሩን መግለፃቸውን ነው ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.