Fana: At a Speed of Life!

2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 610 ኪሎ ግራም ካናቢስ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ ጆባ ቀበሌ 610 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ፡፡

ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ ትላንት ሌሊት 8 ሰዓት ላይ በተካሄደ ኦፕሬሽን ከአንድ ግለሰብ ቤት የተያዘው በህዝብ ጥቆማ እንደሆነ ነው በኢፌዴሪ ጉሙሩክ ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የሻሸመኔ ጉሙሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስተባባሪ ኢንስፔክተር አሰፋ ተርፋሳ የገለጹት።

አደንዛዥ ዕፁ በገንዘብ ሲሰላ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር እንደሚሆንም ነው የተገለጸው።

ኢንስፔክተር አሰፋ ተርፋሳ፥ ማኅበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ኮንትሮባንድን በመከላከል ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፥ አደንዛዥ ዕፅ በሀገር ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያመጣ በመሆኑ ኅብረተሰቡ በቀጣይም ከጸጥታ አካላት ጋር ያላቸውን ትብብር እንዲያጠናክሩ እና ዜጎችን እንዲታደጉ ነው መልዕክት ያስተላለፉት።

የኢፌዴሪ ጉሙሩክ ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በሥድስት ወር ውስጥ ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ሸቀጦችን ይዞ ገቢ ማድረጉንም ኢንስፔክተር አሰፋ ተርፋሳ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በጀማል ከድሮ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.