ግሎባል አሊያንስ ከአማራ ልማት ማኅበር ጋር በመሆን በ10 ሚሊየን ብር የሐይቅ ቁጥር 2 ትምህርት ቤትን ዳግም ሊያስገነቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሎባል አሊያንስ ከአማራ ልማት ማኅበር ጋር በመሆን በሐይቅ ቁጥር 2 ትምህርት ቤት በ10 ሚሊየን ብር ወጪ አራት ህንፃዎችን ለማስገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ።
ወራሪው ኃይል የዕውቀት ማዕድ የሚያቋድሱትን ትምህርት ቤቶች ቢያወድምም በመተባበር ከቀደመው አገልግሎታቸው የተሻለ በማድረግ እንገነባቸዋለን ሲል አርቲስት ታማኝ በየነ ገልጿል።
የአማራ ልማት ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ አልማ ማኅበረሰቡን በማስተባበር የወደሙ የትምህርት ተቋማትን ይገነባል ብለዋል።
ተመሳሳይ የተቋማት ግንባታ በስምንት ዞኖች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የተመለከተው።
በእሸቱ ወልደሚካኤል